• የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

  • By: SBS
  • Podcast

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

By: SBS
  • Summary

  • ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።
    Copyright 2024, Special Broadcasting Services
    Show More Show Less
activate_samplebutton_t1
Episodes
  • "መጪው ዓመት ሁላችንም የምንመኘውን የምናገኝበት አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
    Sep 9 2024
    ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ የግለ ታሪክ ወጉን የሚቋጨው የባሕር ማዶኛ የጥበብ ባለሙያዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳትና ለአዲሱ ዓመት 2017 ያለውን መልካም ምኞት በመግለፅ ነው።
    Show More Show Less
    17 mins
  • ፍቅር ላይ መውደቅ፤ ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናና ድምፃዊት ብፅዓት ስዩም
    Sep 8 2024
    ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት የግለ ታሪክ ወጎቹ ከውልደት ቀዬው ተነስቶ የቲአትር መድረኮች ግዝፈቱ ላይ አላበቃም። ከቶውንም የቲአትር መድረክ ድምፃዊት ብፅዓት ስዩምን እንደምን የሕይወት ምሰሶው አድርጎ መርቆ እንደሰጠውና ለ26 ዓመታት አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ እየኖሩ እንዳለ አሰናስሎ ያወጋል።
    Show More Show Less
    26 mins
  • "ከሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ጋር መሥራት ትምህርት ቤት እንደመግባት የሚቆጠር ነው፤ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
    Sep 3 2024
    ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት ሁለት ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከውልደትና ዕድገቱ አንስቶ፣ በኢትዮጵያ የተውኔት ሕይወት መድረክ እንዴት እንዳበበት፤ የግለ ሕይወት ታሪኩን ነቅሶ በምናባዊ ምልሰት አጓጉዞናል። በቀጣዩ ዝግጅት አብቦና ጎምርቶ እንደምን መድረክ ላይ ግዘፍ እንደነሳ ቀንጭቦ ያወጋል።
    Show More Show Less
    13 mins

What listeners say about የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

Average customer ratings

Reviews - Please select the tabs below to change the source of reviews.