• "መጪው ዓመት ሁላችንም የምንመኘውን የምናገኝበት አዲስ ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
    Sep 9 2024
    ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ የግለ ታሪክ ወጉን የሚቋጨው የባሕር ማዶኛ የጥበብ ባለሙያዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በማንሳትና ለአዲሱ ዓመት 2017 ያለውን መልካም ምኞት በመግለፅ ነው።
    Show More Show Less
    17 mins
  • ፍቅር ላይ መውደቅ፤ ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃናና ድምፃዊት ብፅዓት ስዩም
    Sep 8 2024
    ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት የግለ ታሪክ ወጎቹ ከውልደት ቀዬው ተነስቶ የቲአትር መድረኮች ግዝፈቱ ላይ አላበቃም። ከቶውንም የቲአትር መድረክ ድምፃዊት ብፅዓት ስዩምን እንደምን የሕይወት ምሰሶው አድርጎ መርቆ እንደሰጠውና ለ26 ዓመታት አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ እየኖሩ እንዳለ አሰናስሎ ያወጋል።
    Show More Show Less
    26 mins
  • "ከሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ጋር መሥራት ትምህርት ቤት እንደመግባት የሚቆጠር ነው፤ ሙሉ ሰው ያደርጋል" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
    Sep 3 2024
    ተዋናይ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ ቀደም ባሉት ሁለት ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከውልደትና ዕድገቱ አንስቶ፣ በኢትዮጵያ የተውኔት ሕይወት መድረክ እንዴት እንዳበበት፤ የግለ ሕይወት ታሪኩን ነቅሶ በምናባዊ ምልሰት አጓጉዞናል። በቀጣዩ ዝግጅት አብቦና ጎምርቶ እንደምን መድረክ ላይ ግዘፍ እንደነሳ ቀንጭቦ ያወጋል።
    Show More Show Less
    13 mins
  • "በ'ውጫሌ ውል' ተውኔት መክፈቻና መዝጊያ ወቅት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከሕዝቡ ልብ ውስጥ ፈንቅሎ የወጣ የጋለ ሀገራዊ ስሜት ነበር" ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና
    Aug 27 2024
    ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና፤ በቀዳሚ ክፍለ ዝግጅታችን ውልደትና ዕድገቱን፣ የቀለም ትምህርትና የትወና ጅማሮውን ነቅሶ ግለ ታሪኩን በከፊል አውግቷል። ወደ ቀጣዩ ግለታሪክ ትረካው ያመራው እንደምን ከአንጋፋ የጥበብ ሰዎች ጋር ለመድረክ እንደበቃ በማንሳት ነው።
    Show More Show Less
    17 mins
  • ተዋናይ ተስፋዬ ገብረሃና፤ ከወላይታ እስከ አውስትራሊያ
    Aug 22 2024
    ተዋናይ፣ ደራሲ፣ አዘጋጅና ዳይሬክተር ተስፋዬ ገብረሃና ከስመ ገነን የተውኔት ተጠባቢዎች አንዱና ተጠቃሽ ነው። በሀገረ አውስትራሊያ ከቤተሰቡ፤ በሀገረ ኢትዮጵያ ከትወና ጋር ተዋድዶና ተዛንቆ አለ።
    Show More Show Less
    16 mins
  • "ለመላ ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ ዓመት የምመኘው አንድነትን ነው፤ አንድ ካልሆኑ ዕድገት የለም፤ አንድነት ኃይል ነው" እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን
    Aug 13 2024
    እማማ አኒ ማርሴሩ አታሜይን፤ ቦርቀው ያደጉባት፣ ፊደል የቆጠሩባት፣ ተኩለው የተዳሩባትንና ልጆች ያፈሩባትን ሀገረ ኢትዮጵያ ለቅቀው ከወጡ የአንድ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዕድሜ አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ፍቅረ ነበልባል ግና አሁንም ድረስ ልባቸው ውስጥ ይንቦገቦጋል፤ ትዝታዎቿም ዓመታት ሳያደበዝዟቸው ግዘፍ ነስተው ከአዕምሯቸው ተቀርፀው አሉ።
    Show More Show Less
    18 mins
  • "ለስደት ፍቅሩ የለኝም፤ አውስትራሊያ የመጣሁት አጋጣሚዎች ስላስገደዱኝ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ ሳልመለስ በፊት ወድጄው የኖርኩበት ሀገር ነው" ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ
    Jul 28 2024
    ወ/ሮ ነኢማ ሙዘይን መሐመድ፤ ለአዕምሮ ሕመምተኞች አገልግሎት ሰጪ የሆነው ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። ከውልደትና ዕድገታቸው እስከ በጎ አድራጎት ድርጅት ምሥረታ ያለ የሕይወት ጉዟቸውን ነቅሰው ይናገራሉ።
    Show More Show Less
    15 mins
  • የስደተኞች ሳምንት 2024፤ ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" - ከአፍሪካ ቀንድ እስከ እስያ ፓስፊክ
    Jun 21 2024
    የዓለም የስደተኞች ቀን ከ2001 አንስቶ ወርሃ ጁን በገባ በ20ኛው ቀን ሲከበር፤ አውስትራሊያ ውስጥ ጁን 20ን አካትቶ ከአንድ ቀን መታሰቢያነት ዝለግ ብሎ ከጁን 16 እስከ 22 አንድ ሳምንት ደፍኖ ይከበራል። ይህንኑ አስባብ አድርገን ከሶማሊያ ተንስቶ፣ በኬንያና ኒውዝላንድ አቋርጦ አውስትራሊያ የሠፈረውን ድምፃዊ ኤልያስ የማነ "ኪዊ" ከቀደም የግለ ታሪክ ወጉ ቀንጭበን አቅርበናል።
    Show More Show Less
    19 mins