• ክፍል 26 - የአይሀን ስንብት
    Sep 22 2009
    የሚያሳዝን ዜና ፦ ባልደረባ አይሀን ወደ ቱርክ ስለሚሄድ ይሰናበታል። ምንም እንኳን የተቀሩት ባልደረቦች ለስንብቱ ስጦታ ቢያዘጋጁም ተደስተው ማክበር ግን አልቻሉም። ፓውላ ጠዋት ወደ ቢሮ እንደመጣች ወዲያው ፓርቲ ማዘጋጀት አለባት። የፓርቲው ምክንያት ግን አላስደሰታትም። አይሀን የ Radio D ዝግጅት ክፍልን ለቆ ወደ ቱርክ አባቱን ለመርዳት ይሄዳል። በስንብቱ ላይም አጭር ንግግርና ጓደኛውን ኡላሊያ የሚያስታውስበት ስጦታ ለአይሀን ይሰጡታል። ለበዐሉ ስንብት ሲሉ ፕሮፌሰሩ በዚህ ምዕራፍ ስለ ሰዋሰው አይመለከቱም። ሆኖም የተወሰነ ነገሮች እንዴት ዋና ቃላቶች እንደሚዋኀዱ ከማለት ወደ ኋላ አይሉም።
    Show More Show Less
    15 mins
  • ክፍል 25 - የመርከቦች ሰላምታ
    Sep 22 2009
    ጋዜጠኞቹ "getürkt" የሚለውን ቃል ትርጉም እያፈላለጉ ነው። በተጨማሪም አስገራሚ የሆነ ወደብ ይጎበኛሉ። እዛም እያንዳንዱ መርከብ በተለየ ሁኔታ ሰላምታ ይሰጠዋል።ቪልኮም ሆፍት በተባለው ወደብ እያንዳንዱ መርከብ በክፍለ ሀገሩ ብሔራዊ መዝሙር ሰላምታ ይሰጠዋል። የክፍለ ሀገራቸውን ባንዲራ እያውለበለቡ ይሄዳሉ። በአንድ የማድመጥ ትምህርት ላይ ፊሊፕና ፓውላ የዚህን የስራ ዘርፍ በትክክል ይመለከታሉ። "getürkt" የሚለው ቃል ትርጉምም ከዚህ ስራ ጋር ይገነኛል። የዝግጅት ክፍል ደግሞ አይሀን የረፍት ጊዜውን ስለ ጉጉቶች መፅሀፍ በማንበብ ያሳልፋል። ኡሌሊያ ማንበብ ስለማትችል አይሀን ያነብላታል። ይህም ምዕራፍ የተሳቢ ግሶችን ይመለከታል። አንድ ግስስ እንዴት በተሳቢው አማካይነት ይቀየራል?
    Show More Show Less
    15 mins
  • ክፍል 24 - የ ሀንቡርግ ጋዜጣ
    Sep 22 2009
    ጉጉት ኡላሊያ ጋዜጠኞቹን ወደ ትክክለኛው መስመር ትመራቸዋለች። እነሱም የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች እጅ ሳይኖርበት እንደማይቀር ይደርሱበታል። ፊሊፕ የሚያደርገውም አስተያየት ፓውላ ትደነግጣለች። የሀንቡርግ ጋዜጣ አዘጋጆች አውቀው ባህር ዳር ታየ የተባለውን የአሳ ነባሪ ታሪክ ፈጥረው እንደፃፉ ፓውላ ፣ ፊሊፕና ኡላሊያ ይደርሱበታል። ይህንንም ያደረጉት የአንባቢያቸውን ቁጥር ለመጨመር ሲሉ ነው። በኋላም ፊሊፕና ፓውላ በሆነ በአንድ ቃል አጠቃቀም ይጣላሉ። ፊሊፕም ፓውላ እንድትረጋጋ ሲል የወደቡ እንኳን ደህና መጡ መቀበያ ጋር ይጋብዛታል። ፊሊፕ ለሚለው ነገር ተጠንቅቆ ቢሆን ኖሮ ፓውላን ባላስቆጣት ነበር። በተረፈ የሚነጠሉ ግሶችን እናያለን። አንዳንድ የግስ ተሳቢዎች የግሱን ትርጉም የበለጠ ያብራራሉ። አልፎ አልፎም ግሱን ከተሳቢው ነጥሎ በቅድመ ቃል መልክ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ምዕራፉ ይመለከታል።
    Show More Show Less
    15 mins
  • ክፍል 23 - አንድ የአሳ ነባሪ ክንፍ ያደረገ የባህር ውስጥ ጠላቂ
    Sep 22 2009
    ፓውላና ፊሊፕ አሳ ነባሪ የተባለውን ወሬ ይደርሱበትና የታሪኩን ውሸት ይፈታሉ። ያልተፈታው ነገር ግን ለምን ይህ እንደተደረገ ነው። ወዲያው ሳይጠብቁ ከጉጉት ኡላሊያ እርዳታ ያገኛሉ። የተሰወረውን የባህር ተንሳፋፊ ፓውላና ፊሊፕ እየፈለጉ ሳለ የባህር ውስጥ ጠላቂው ከተባለው አሳ ነባሪ ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ይገምታሉ። የባህር ውስጥ ጠላቂው ጀርባው ላይ የአሳ ነባሪ ክንፍ አድርጎ መላውን የሀንቡርግ ከተማ ለፍርሀትና ለድንጋጤ ጥሏል። ግን ለምን ይህን ያደርጋል? በሀንቡርግ ከተማ በመሀል ብቅ ያለችው ኡላሊያ ነገሩን ልታብራራ ትችላለች። እሷም አዲስ ግኝት አድርጋለች። ኡላሊያ አሁን በምታደርገው ጉብኝት የሀላፊ ጊዜያትን የአጠቃቀም ዘዴ ( Vergangenheitsform ) መመልከት ይቻላል። በተጨማሪ የበለጠ ትኩረት የሚሰጣቸው የቅርብ ሀላፊ ጊዜ አጠቃቀምን ነው።
    Show More Show Less
    15 mins
  • ክፍል 22 – የተሰወረው የባህር ተንሳፋፊ
    Sep 22 2009
    ፊሊፕና ፓውላ ስለ አካባቢው አንድ ፍንጭ ለማግኘት ጉዞ ይጀምራል። እነሱም አዳዲስ የሚገርሙ ግኝቶች ያደርጋሉ፦ ሰርፈረኛ የሌለበት የሰርፍ ጣውላ እና ግራ የሚያጋባ የጋዜጣ ፁሁፍ ትኩረታቸውን ያጠናክረዋል። ከስፍራው ትንሽ ራቅ ብሎ ሁለት ጋዜጠኞች ስለ አስገራሚው አሳ ነባሪ ያፈላልጋሉ። አንድ የባህር ተንሳፋፊ የሌለበት የሰርፍ ጣውላ ክፉ ነገር ሳይከሰት እንዳልቀረ ያመለክታል። በኋላም የሀምቡርግ ጋዜጣ ላይ የተባለውን አሳ ነባሪና የፊሊፕና የላውራን ፎቶ ያገኛሉ። ሁለቱም በፍርሀት ይመለከቱ ነበር። ግን ይሄ ሁላ እንዴት አንድ ላይ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል? ቢያንስ ሰዋሰውን ስንመለከት ትርጉም የሚሰጡ ነገሮች አሉ። ይህ ምዕራፍ የበለጠ ትኩረት የሚሰጠው "sie" እና "er" ለሚሉት ተወላጠ ስሞች ነው። ከዚህ በፊት በነበረው ክፍል የተመለከትናቸውን አርቲክሎች ከዋናው ቃል ጋር መዛመድ ያስፈልጋል።
    Show More Show Less
    15 mins
  • ክፍል 21 - አንድ አሳ ነባሪ በሀንቡርግ ከተማ
    Sep 22 2009
    በ Radio D ዝግጅት ክፍል ያለው አስቀያሚ ያየር ጠባይ ነው። ወደ ባህር አካባቢ የሚያስልክ የምርምር ትዕዛዝ በአሁን ሰዐት አስደሳች ነው። ፊሊፕና ፓውላ ወደ ሀንቡርግ ለዚሁ ጉዳይ ይሰደዳሉ። እዛም አንድ አሳ ነባሪ የወደቡ አፋፍ ላይ ሳይንጎራደድ አይቀርም። ፓውላ ፣ ፊሊፕና አይሀን ቀላል ጊዜ አይደለም የሚጠብቃቸው። በቢሮ ውስጥ ያለው ሙቀት የሚቻል አይደለም። ክፍሉ ደግሞ ማቀዝቀዛ እንኳን የለም። የፓውላ ወደ ባህር ወይም ውቅያኖስ ለመሄድ መመኘት ኮምፑን በትንሹም ቢሆን ያረካል። ጋዜጠኞቹ አሳ ነባሪ ወደታየበት የሀንቡርግ ወደብ መጓዝ አለባቸው። አሳ ነባሪ የተባለውን ያዩት የሰዎች ብዛት ሲታይ ሁለቱ ጋዜጠኞች ምንም ሊያመልጣቸው አይችልም። ይህ ለፕሮፌሰሩም ከባድ ነው። የ ተባዕት ፆታ አርቲክል የቀጥተኛ ተሳቢ መምንጠቀምበት ጊዜ፤ የቃሉ ማብቂያ እንዴት እንደሆነ ለማብራራት ፕሮፌሰሩ ብዙ መጣር አለበት። "kein" የሚለው አፍራሽ ቃል ከዋናው ቃል ጋር መዋኸድ አለበት።
    Show More Show Less
    15 mins
  • ክፍል 20 - የአድማጮች መጠይቅ
    Sep 22 2009
    ፊሊፕና ፓውላ አድማጮቹ ያላቸውን አስተያየት ይጠይቃሉ። የ መርሀ ግብሩ ጭብጥ ውሸት ሀጢያት ሊሆን ይችላልን? "Kann denn Lüge Sünde sein?" ይሰኛል። እዚህ ጋር አድማጮች ስለ ውሸተኞቹ ክብ የበቆሎ ቆረኖች የሚያስቡትን መናገርና በተጨማሪም የገበሬዋቹን እርምጃ መገመት ይችላሉ። ውሸት ሀጢያት ሊሆን ይችላልን? "Kann denn Lüge Sünde sein?" ፊሊፕና ፓውላ ዛሬ አድማጮችን የሚጠይቁት ጥያቄ ነው። መነሻው ሁለቱ ጋዜጠኞች የዘገቡባቸው ክብ የበቆሎ ቆረኖች ናቸው። ይህ የገበሬዎቹ ማታለል ፤ ጎጂ አልያስ የገራገር ጎብኝዎቹ የግል ጥፋት ነው? ግን የአድማጮች መልስ ግልፅ ነው። የጋዜጠኞቹን ጥያቄ አዎ አልያም አይደለም በሚል ከሚመልሱት አድማጮች ባሻገር ፕሮፌሰሩ ሶስት አማራጭ መልሶች ያሉትን መጠይቅ ያዘጋጃል። በጀርመንኛ ቋንቋ ከአንስታይ (Femininum) እና ተባዕት ፆታ (Maskulinum) ባሻገር ሶስተኛ ከሁለቱም ያልሆነ ፆታ Neutrum አለ። እነዚህም "der", "die" እና "das" በተሰኙ አርቲክሎች ይብራራሉ።
    Show More Show Less
    14 mins
  • ክፍል 19 - ውሸቱ ተጋለጠ
    Sep 22 2009
    ምንም እንኳን ክብ የበቆሎ ቆረኖቹን ገበሬዎቹ ቢሆኑም ያደረጉት ኡላሊያ ግን ኡፎዎች ይኖራሉ ብላ ታምናለች። ፓውላና ፊሊፕ የሰፈሩን ነዋሪዎች ሲጠይቁ ስለ ክቡ የበቆሎ ቆረኖች ውሸት ይሰሙና ወደ መጠጥ ቤት ያመራሉ።ፓውላና ፊሊፕ የክቡን የበቆሎ ቆረኖች ውሸት ያረጋግጣሉ። ግን ኡፎዎች ምናልባት ይኑሩ አይኑሩ  እርግጠኛ አይደሉም። ለመሆኑ UFO ሲተነተን ምንድን ነው? ስለዚያ ኡላሊያ ልታብራራ ትችላለች። ይህ ብቻ ሳይሆን ከኡፎዎቹ  አንድ ሳታይ እንደማትቀር እርግጠኛ ነች። በመጨረሻም ሁለቱ ጋዜጠኖች በመንደሩ መጠጥ ቤት የሚገኙትን እንግዶች ስለ ክብ የበቆሎ ቆረኖቹ ውሸት የሚያስቡትን ይጠይቃሉ።  ይህ የመጠጥ ቤቱ እንግዶች ትውስታ ሀላፊ ጊዜን (Präteritum) ለመጠቀም ጥሩ አጋጣሚ ነው። ሀላፊ ጊዜው መደበኛ ያልሆነው የመሆን ግስን unregelmäßige Verb "sein"  ያካትታል በተጨማሪም "können" የሚለው ግስ  በድጋሚ ይብራራል።  ትኩረት መሰጠት የሚገባው ሌላው እንዴት የአንድ ግስ መሰረት የአነባቢ ፊደሎቹን እንደሚለውጥ ነው።
    Show More Show Less
    15 mins