• የዓለም ዜና

  • By: DW
  • Podcast

የዓለም ዜና

By: DW
  • Summary

  • ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
    2025 DW
    Show More Show Less
Episodes
  • የጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    Jan 15 2025
    ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አፍሪካ ሕብረት ቅርንጫፍ ከ6 ሚሊየን ዶላር በላይ «በሀሰተኛ ሰነድ» ለማውጣት ሙከራ እድርገዋል በሚል የሙስና እና ከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ጥፋተኛ ተባሉ። የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድቤት አምስት የከተማዋ ትምህርት ቤቶች በሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የጣሉት ክልከላ ታግዶ እንዲቆይ ወሰነ። ዴሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ ወርቅ እና በርካታ ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ይዘዋል በሚል የተከሰሱ ሦስት ቻይናውያን ሰባት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው። ከሥልጣናቸው በግዳጅ እንዲነሱ ግፊት የተደረገባቸው የደቡብ ኮርያ ፕሬዝደንት ታሠሩ።
    Show More Show Less
    10 mins
  • የጥር 6 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    Jan 14 2025
    -የአፋር ክልልን በመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ሰዎች በቂ ዕርዳታ እንዳላገኙ አስታወቁ።በመሬት መንቀጥቀጡ ከተጎዱ አካባቢዎች ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።ተፈናቃዮቹና ርዳታ አቀባዮች እንደሚሉት የምግብ፣የመድሐኒትና የመጠለያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።----የሶማሊያ የፀጥታ ኃይላት በሐገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት ሸምቀዉ ነበር ያሏቸዉን የእስላማዊ መንግስት (IS) ታጣቂዎች መግደላቸዉን አስታወቁ።-የእስራኤልና የሐማስ ተደራዳሪዎች ጋዛን የሚያወድመዉን ጥቃት ለማቆምና ታጋቾችን ለመልቀቅ የሚረዳ ስምምነት ለማድረግ መቃረባቸዉ እየተነገረ ነዉ።
    Show More Show Less
    10 mins
  • DW Amharic የጥር 05 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    Jan 13 2025
    የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት “የሲቪክ ምኅዳሩን የሚያጠቡ እርምጃዎች ከመዉሰድ በመቆጠብ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት በተደነገገው መሠረት ለመደራጀት መብት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲያረጋግጥ” 50 የመብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠየቁ። በጦርነት ከቀያቸው ተፈናቅለው በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የተጠለሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሔዱ። በናይጄሪያ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን የወገኑ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 40 ገበሬዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ። ቃጣር የጋዛን ጦርነት ለማብቃት የተዘጋጀ ሥምምነት የመጨረሻ ረቂቅ ለእስራኤል እና ለሐማስ ተደራዳሪዎች አቀረበች።
    Show More Show Less
    10 mins

What listeners say about የዓለም ዜና

Average customer ratings

Reviews - Please select the tabs below to change the source of reviews.